Public Funding for the Culture and Creative Sector in Ethiopia - CfCA Ethiopia #2
ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ - Connect for Culture Africa - Ethiopia
Release Date: 05/16/2025
ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ - Connect for Culture Africa - Ethiopia
ክፍል 3፡ የባህል ሚና ለሰላም, ሰብዓዊ መብት እና ዲሞክራሲ ግንባታ በዚህ ክፍል የባህል ተመራማሪ ከሆኑ ዶ/ር ጥላሁን በጅቷል ጋር ኪነ-ጥበብ፣ባህል እና ፈጠራ በሰላም ግንባታ፣ሕብረተሰብ ላይ ተሃድሶ በመፍጠር እንዲሁም በብሔራዊ ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ምን አይነት ሚና እንደሚጫወቱ እንዳስሳለን፡፡ ከባህላዊ ትሩፋቶች እስከ ዘመናዊ ኪነ-ጥበብ ድረስ ያሉትን ሁኔታዎች...
info_outlineሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ - Connect for Culture Africa - Ethiopia
ባህል እና የባህል እና ፈጠራ ኢንዱስትሪው ላይ ለካበተ እና ጥልቅ ውይይት መድረክ በሆነው የሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት 3ኛ ክፍል ባህል ለስራ እድል ፈጠራ ያለው ሚና የሚል ውይይት ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ በተሾመ ወንድሙ ተዘጋጅቶ የሚቀርበው እና የእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ያለው ይህ ክፍል በባህል እና በስራ ቅጥር መካከል ያለውን ወሳኝ ሚና ይዳስሳል፡፡የባህል...
info_outlineሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ - Connect for Culture Africa - Ethiopia
የሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት ሁለተኛው ክፍል ‘የመንግስት ድጋፍ ለባህል’ የሚል ሲሆን- በባህል እና የባህል እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ላይ የካበቱ እና ጥልቀት ያላቸው ውይይቶች የሚካሄዱበት መድረክ ነው፡፡ በተሾመ ወንድሙ ተዘጋጅቶ ከእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ጋር የሚቀርበው ይህ ክፍል በኢትዮጵያ እንዲሁም ከዛም ባሻገር ኪነ-ጥበብን ለመደገፍ የመንግስት ድጋፍ...
info_outlineሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ - Connect for Culture Africa - Ethiopia
የባህል ምንነት እና ፋይዳው የሚለው የመጀመሪያ ክፍል የፖድካስት ዝግጅት የሲኤፍሲኤ ፖድካስት ተከታታይ ክፍሎችን መክፈቻ ዝግጅት ሲሆን ይህ ፖድካስት በባህል እና በባህላዊ እና ፈጠራ ኢንዱስትሪው ላይ ላተኮሩ የካበቱ እንዲሁም ጥልቅ ምልከታን የያዙ ውይይቶች የሚንጸባረቁበት መድረክ ነው፡፡ በዚህ በተሾመ ወንድሙ አቅራቢነት በሚቀርበው እና የእንግሊዝኛ የግርጌ...
info_outlineየሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት ሁለተኛው ክፍል ‘የመንግስት ድጋፍ ለባህል’ የሚል ሲሆን- በባህል እና የባህል እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ላይ የካበቱ እና ጥልቀት ያላቸው ውይይቶች የሚካሄዱበት መድረክ ነው፡፡
በተሾመ ወንድሙ ተዘጋጅቶ ከእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ጋር የሚቀርበው ይህ ክፍል በኢትዮጵያ እንዲሁም ከዛም ባሻገር ኪነ-ጥበብን ለመደገፍ የመንግስት ድጋፍ እንዴት እንደሚመደብ ይዳስሳል፡፡በባህል ላይ የመንግስት ኢንቨስትመንት ምን ይመስላል? ተስፋ ሰጪ የሆኑ አዳዲስ ክንውንኖች ምንድን ናቸው፤ክፍተቶችስ ያሉት እምን ጋ ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች ይመለከታል፡፡
ይህንን ውይይት የሚቀላቀሉት ዶ/ር ይስማ ጽጌ ሲሆኑ ጥናታዊ ምርምር ስራዎችን የሚሰሩት ዶ/ር ይስማ በቅርብ ጊዜ የሰሩት ጥናት በባህል ዘርፉ ላይ የመንግስት የገንዘብ ድጋፍ ምን ይመስላል የሚለው ላይ የብርሃን ጮራን የሚፈነጥቅ ነው፡፡ አቶ ተሾመ እና ዶ/ር ይስማ በጋራ የዚህን ጥናት መረጃ በጥልቀት ይመለከታሉ፣ዘላቂ የገንዘብ ድጋፍ እንዳይኖር የሚያደርጉ እንቅፋቶች እንዲሁም የለውጥ መንገዶችም ላይ ይወያያሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ https://cfcafrica.org
Hosted by Teshome Wondimu and subtitled in English, this episode explores how public funds are allocated to support the arts in Ethiopia and beyond. What does government investment in culture look like? What are the promising developments—and where do the gaps remain?
Joining the conversation is Dr. Yisma Tsige, a researcher whose recent work shines a light on public financing within the cultural sector. Together, they delve into the data, discuss the barriers to sustainable funding, and highlight pathways for progress.
Tune in and explore more at https://cfcafrica.org